You are on page 1of 17

ስለ ቀጠሮ ማክበር መጠይቅ፤

በ www.tatariw.org

ትንሽ ስለቀጥሮና መጠይቁ አጭር ማብራሪያ፤ 19/06/2010


ባጭሩ ቀጠሮ ማክበር ጊዜን በትክክል ተጠቅሞ ውጤታማ እንድንሆን ያደርጋል። ምክንያቱም
ቀጠሮ ከቦታና ከሰአትም አልፎ ክብርን፣ ማክበርን፣ እቅድን፣ በቃል መገኘትንና ማንነትን ማሳያ
ትልቅ አጋጣሚ ስለሆነ ነው፡፡ በቀጠሮ ምክንያት ወዳጅ ጋር ልንቀያየም እንችላለን፡፡ በቀጠሮ
ምክንያት በህይወታችን ውስጥ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ልናጣ እንችላለን፡፡ ስለዚህ ግለሰብም ሆነ
ህብረተሰብ ማንኛውንም ቀላልም ሆነ ከባድ ነገር በግዜው መፈጸም ከቻለ ውጤታማ ሊሆን
ስለሚችል የዜጋና የሃገር እድገትንም ያፋጥናል።

ታዲያ ቀጠሮ አለማክበር በተለይ በአፍሪቃውያን ዘንድ የተለመደ ነው። ቀጠሮ አለማክበር
ኢትዮጵያውያንም ላይ ጎልቶ ይታያል። ይህ መጠይቅ ሳይንሳዊ ባይሆንም ኢትዮጵያውያን ስለ
ቀጠሮ ያላቸውን አስተያየት እንዲሰጡ የተዘጋጀ መጠይቅ ነው። መጠይቁም የተዘጋጀው ስለ
አጠቃላይ ቀጠሮ እንጂ ስለተወሰነ ቀጠሮ ለምሳሌ የስብሰባ ቀጠሮ፣ የሰርግ ቀጠሮ ወዘተ ተብሎ
አይደለም። ሆኖም ግን ከመጠይቁ መልስ በመነሳት የሆነ ውጤት ላይ መድረስ እንደሚቻል ግልጽ
ነው። ከታች ሲያነቡ እንደሚያገኙት በዚህ መጠይቅ ውስጥ፤ 139 ሰዎች ተሳትፈው 96ቱ ሙሉ
በሙሉ ሲመልሱ 43ቱ ግን በተለያዬ ምክንያት ሳይጨርሱ አቋርጠዋል። ስለዚህ ውጤቱ መሰረት
የሚያደርገው ሙሉ በሙሉ በመለሱት በ96ቱ ላይ ይሆናል።

ይህ መጠይቅ በውጭ ሃገር ውስጥ (በተለይ ኖርዌይ) ውስጥ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተደረገ
ነው። በርግጥ ኢንተርኔት ላይ ሰፍሮ ስለነበር ኢትዮጵያ ውስጥም የሚኖሩ መልሰው ይሆናል።
ከሌላም አገሮች እንደዚሁ። ኖርዌይ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በብዛት ስለመለሱ በጣም
አድንቄያቸዋለሁ! ያለነሱ ተሳትፎ ከዚህ ውጤት ላይ መድረስ አይቻልም ነበር።

የዚህ መጠይቅ ሰነድ የሚከተሉትን መረጃዎች ይዟል፤


➢ ትንሽ ስለቀጥሮና መጠይቁ አጭር ማብራሪያ፤ (ከላይ እንደተጠቀሰው)
➢ የመጠይቁ ውጤትና ቁጥሮቹን እንዲረዱ መመሪያ፤
➢ የያንዳንዱ ጥያቄ መልስና ውጤት በቁጥርና በግራፍ ከአዘጋጁ አስተያየት ጋር፤
➢ በመጠይቁ መጨረሻ ላይ ከተሳታፊዎች የቀረቡ በርካታ አስተያየቶች፤
➢ ተሳታፊዎች ከዚህ ሀገር ነው የላክነው ባሉት መሰረት የሀገር ዝርዝር ፤
➢ ውጤቱ ኦስሎ ውስጥ ለኢትዮጵያውያን በአካል በቀረበ ጊዜ የቀረቡ አስተያየቶች፤
➢ አስተያየቶቹንና መጠይቁን መሰረት በማድረግ የአዘጋጁ አስተያየትና ምስጋና፤

የመጠይቁ ውጤትና ቁጥሮቹን እንዲረዱ መመሪያ፤


Field summary for 1፤ ለምሳሌ የዋና የጥያቄ ቁጥር 1፣ 2፣ 3 ወዘተ ማጠቃለያ።
Count እና Percentage፤ በአንዱ ጥያቄ ላይ የተሰጠ መልስ ብዛት በቁጥርና በእጅ። የዚህ ቁጥርና
እጅ ብዛት በራሱ አጠቃላይ ውጤት አይሰጥም። ምክንያቱም በአንዱ ዋና ጥያቄ ላይ አንድ ሰው
ከአንድ በላይ የምርጫ መልስ ሰጥቶ ሊሆን ስለሚችል።
የያንዳንዱ ጥያቄ መልስና ውጤት በቁጥርና በግራፍ ከታታሪው አስተያየት ጋር፤
Number of records in this query: 139
Total records in survey: 139
Percentage of total: 100.00%

Field summary for 1


ብዙ ኢትዮጵያውያን ቀጠሮ የማናከብርበት ምክንያት ምንድን ነው ብለው ያስባሉ?
Answer Count Percentage
ቀጠሮ ማክበር የፈረንጆች ስለሆነ። 4 2.88%
ለቀጠሮ ብሎ መጨናነቅ ኣያስፈልግም። 7 5.04%
እራስንና ጊዜን መቆጣጠር ሲያቅት። 34 24.46%
ገደለሽነትና ባጋጣሚ መኖር ስለተለመደ። 46 33.09%
የጊዜ ጥቅሙን ባለመረዳት። 31 22.30%
እንኳን ለቀጠሮ ለነጻነታችንም ዘግይተናል። 13 9.35%
ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን ስለማናከብር። 17 12.23%
መዘግየት ቢያሳፍርም ኢትዮጵያውያንን አይመለከትም። 5 3.60%
ካሁን በኋላ ቀጠሮ አከብራለሁ! 15 10.79%
እኔ ቀጠሮ ስለማከብር ኣይመለከተኝም። 24 17.27%
Other 12 8.63%

50
45
40 ቀጠሮ ማክበር የፈረንጆች ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን
35 ስለሆነ። ስለማናከብር።
30 ለቀጠሮ ብሎ መጨናነቅ መዘግየት ቢያሳፍርም
ኣያስፈልግም። ኢትዮጵያውያንን
25 አይመለከትም።
20 እራስንና ጊዜን መቆጣጠር ካሁን በኋላ ቀጠሮ
15 ሲያቅት። አከብራለሁ!
10 ገደለሽነትና ባጋጣሚ መኖር እኔ ቀጠሮ ስለማከብር
ስለተለመደ። ኣይመለከተኝም።
5
የጊዜ ጥቅሙን ባለመረዳት። Other
0 እንኳን ለቀጠሮ
1 2 ለነጻነታችንም ዘግይተናል።

አስተያየት፣ እንደሚያዩት ከቀረቡት ምርጫወች ውስጥ ግደለሽነትና ባጋጣሚ መኖር ስለተለመደ። እና እራስንና
ጊዜን መቆጣጠር ሲያቅት። በሚለው በከፍተኛ ደረጃ ተመልሰዋል።
Field summary for 2
እርስዎ ቀጠሮ ያከብራሉ?
Answer Count Percentage
ኣዎ ኣከብራለሁ! 66 47.48%
ኣንዳንድ ጊዜ ኣላከብርም። 43 30.94%
ኣይ እኔ ቀጠሮ ኣላከብርም። 1 0.72%
No answer 29 20.86%

70
60
50 ኣዎ ኣከብራለሁ!
40 ኣንዳንድ ጊዜ
ኣላከብርም።
30
ኣይ እኔ ቀጠሮ
20 ኣላከብርም።
10 No answer
0
1 2

አስተያየት፤ ከመልሱ እንደሚያዩት ሰወች በብዛት ቀጠሮ እንደሚያከብሩ መልሰዋል። ይህ በራሱ በጣም ጥሩ ነው።

Field summary for 3


ቀጠሮ ማክበር ምን ማለት ነው ብለው ያስባሉ?
Answer Count Percentage
በቃል መገኘትና ጊዜን በትክክል መጠቀም መቻል። 104 74.82%
በፈለጉበት ጊዜ መድረስ። 6 4.32%
No answer 29 20.86%

120
100
በቃል መገኘትና ጊዜን
80 በትክክል መጠቀም
60 መቻል።
40 በፈለጉበት ጊዜ
መድረስ።
20
No answer
0
1 2

አስተያየት፡ ከላይ እንደሚያዩት መልሱ ግልጽ ነው። ነገር ግን 6 ሰወች ቢሆኑም "በፈለጉበት ጊዜ መድረስ"
ማለታቸው ቅር ያሰኛል።
Field summary for 4
ቀጠሮ ኣለማክበርስ ምን ማለት ነው ብለው ያስባሉ?
Answer Count Percentage
መዋሸትና መወስለት ነው። 90 64.75%
ምንም ኣይደለም፤ ለቀጠሮ ብሎ መጨናነቅ ኣያስፈልግም። 20 14.39%
No answer 29 20.86%

100

80
መዋሸትና No answer
60 መወስለት ነው።
ምንም ኣይደለም፤
40 ለቀጠሮ ብሎ
መጨናነቅ
20
ኣያስፈልግም።
0
1 2

አስተያየት፡ እዚህ ላይ ምናልባት ምርጫወቹ አንስው ይሆናል ግን 20 ወቹ የመለሱትን ሲያዩት አሁንም ያሳስባል።
ቅር ያሰኛል።

Field summary for 5


በተደጋጋሚ ቀጠሮ ላይ የሚዘገይን ኢትዮጵያዊ እንዴት ያዩታል?
Answer Count Percentage
ጊዜውን በትክክል ስላልተጠቀመ እታዘበዋለሁ። 37 26.62%
ጊዜውን መቆጣጠር የማይችል ሰነፍ ነው። 35 25.18%
ለጊዜ ምንም ደንታ የሌለውና ባጋጣሚ የሚኖር ነው። 56 40.29%
ምክንያት የሚያበዛ ውሸታም ነው። 33 23.74%
ክብር ኣይገባውም። 22 15.83%
እንደዚህ እየዘገየ ሌላውንም የህይወቱን ክፍል እንዴት እንደሚኖር ኣይገባኝም። 25 17.99%
በቀላል ነገር ስለማይለማመድ ለነጻነቱም ቢሆን የዘገየ ነገር ነው። 22 15.83%
በተደጋጋሚ ቢዘገይም ምንም ኣይደለም። 1 0.72%
60

50 ጊዜውን በትክክል ስላልተጠቀመ ክብር ኣይገባውም።


እታዘበዋለሁ።
40 ጊዜውን መቆጣጠር የማይችል እንደዚህ እየዘገየ ሌላውንም
ሰነፍ ነው። የህይወቱን ክፍል እንዴት
30 እንደሚኖር ኣይገባኝም።
ለጊዜ ምንም ደንታ የሌለውና በቀላል ነገር ስለማይለማመድ
20 ባጋጣሚ የሚኖር ነው። ለነጻነቱም ቢሆን የዘገየ ነገር
ነው።
10
ምክንያት የሚያበዛ ውሸታም በተደጋጋሚ ቢዘገይም ምንም
0 ነው። ኣይደለም።
1 2

አስተያየት፤ በዛ ያሉ ምርጫወች ቢሰጡም "ለጊዜ ምንም ደንታ የሌለውና ባጋጣሚ የሚኖር ነው። " ያሉት ብዛት
አላቸው።
Field summary for 6
እርስዎ ቀጠሮው ሰዓት ላይ ደርሰው ሌሎች ሲዘገዩ ምን ይሰማዎታል።
Answer Count Percentage
የተለመደ ስለሆነ እጠብቃለሁ። 30 21.58%
ኣሁንስ የዘገዩት እስከሚመጡ መጠበቅ ሰልችቶኛል። 20 14.39%
በሰዓቱ መጥቼ የዘገዩትን ላለመጠበቅ እኔም መዘግዬት እመርጣለሁ። 14 10.07%
የማህበራዊ ግንኙነቴን ቀንሶታል። 20 14.39%
ቀጠሮን በተመለከተ ሰዎች ኣይገባቸውም። 10 7.19%
ያለበቂ ምክንያት የሚዘገይ ሰውን ሁለተኛ ለመቃጠር ኣላምነውም። 58 41.73%
Other 6 4.32%
70
60 የተለመደ ስለሆነ የማህበራዊ ግንኙነቴን Other
50 እጠብቃለሁ። ቀንሶታል።
40 ኣሁንስ የዘገዩት ቀጠሮን በተመለከተ ሰዎች
እስከሚመጡ መጠበቅ ኣይገባቸውም።
30 ሰልችቶኛል።
20 በሰዓቱ መጥቼ የዘገዩትን ያለበቂ ምክንያት የሚዘገይ
10 ላለመጠበቅ እኔም ሰውን ሁለተኛ ለመቃጠር
መዘግዬት እመርጣለሁ። ኣላምነውም።
0
1 2

አስተያየት፤ ያለበቂ ምክንያት የሚዘገይ ሰውን ሁለተኛ ለመቃጠር አላምነውም ያሉት በርካታ ናቸው።

Field summary for 7


እክል ገጥሞዎት በቀጠሮ ከዘገዩ ምን ያደርጋሉ?
Answer Count Percentage
እድሉ ካለ ደውዬ ከይቅርታ ጋር እንደምዘገይና መቼ እንደምደርስ ኣሳውቃለሁ። 100 71.94%
ችግር ስለሌለው ቀስ ብዬ እቀጠሮው ቦታ እደርሳለሁ። 2 1.44%
ጉዳዩ ወይም ስብሰባው ሊያልቅ ሲል ብደርስም ምንም ኣይደለም። 0 0.00%
No answer 37 26.62%

120
100 እድሉ ካለ ደውዬ ከይቅርታ ጉዳዩ ወይም ስብሰባው
80 ጋር እንደምዘገይና መቼ ሊያልቅ ሲል ብደርስም
60 እንደምደርስ ኣሳውቃለሁ። ምንም ኣይደለም።
40 ችግር ስለሌለው ቀስ ብዬ No answer
20 እቀጠሮው ቦታ
0 እደርሳለሁ።
1 2

አስተያየት፤ "እድሉ ካለ ደውዬ ከይቅርታ ጋር እንደምዘገይና መቼ እንደምደርስ አሳውቃለሁ። " ብለው የመለሱ በጣም
በርካታ ናቸው። ሆኖም ግን በተለምዶ መዘግየታቸውን ደውለው የሚያሳውቁ ኢትዮጵያውያን ጥቂቶች ናቸው። መጠይቁ
ላይ የተካፈሉት ግለሰቦች ግን ስለቀጠሮ የሚቆረቆሩ መሆናቸውን ያመለክታል።
Field summary for 8
ቀጠሮ ላይ ዘግይተው ሲደርሱ ምን ያደርጋሉ?
Answer Count Percentage
ሰላምም ብዬ ሆነ ዝም ብዬ ፈገግ እያልኩ እደባለቃለሁ። 5 3.60%
ይቅርታ እጠይቃለሁ። 90 64.75%
በስኣቱ ኣለመድረስ ምንም ይቅርታ ማለት ኣያስፈልገውም። 2 1.44%
ኣፍራለሁ። 5 3.60%
No answer 37 26.62%

100
80 ሰላምም ብዬ ሆነ ዝም ኣፍራለሁ።
ብዬ ፈገግ እያልኩ
60 እደባለቃለሁ።
40 ይቅርታ እጠይቃለሁ። No answer
በስኣቱ ኣለመድረስ
20 ምንም ይቅርታ ማለት
0 ኣያስፈልገውም።
1 2

አስተያየት፤ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተካፋዮች ቀጠሮ ላይ ዘግይተው ሲደርሱ ምን አንደሚሰማቸው ከላይ ግልጽ
ነው። 5 ሰወች ደግሞ "ሰላምም ብዬ ቢሆን ዝም ብዬ ፈገግ እያልኩ እደባለቃለሁ።" ብለው መመለሳቸው ትንሽ የሚገርም
ነው?

Field summary for 9


ከፈረንጅ ጋር ከሆነ ኢትዮጵያዊ ቀጠሮ ያከብራል?
Answer Count Percentage
ኣዎ ያከብራል። 93 66.91%
ኣይ ኣያከብርም። 9 6.47%
No answer 37 26.62%

ኣዎ ያከብራል።
ኣይ ኣያከብርም።
No answer

አስተያየት፤ ኢትዮጵያዊ ከፈረንጅ ጋር ቀጠሮ ካደረገ ቀጠሮውን ያከብራል ብለው የሚያስቡት እጅግ በጣም ብዙ
ናቸው። ይህ ማለት ከአንድ ኢትዮጵያዊ ጋርና ከፈረንጅ ጋር መቃጠር በራሱ ልዩነት አለው ማለት ነው።
Field summary for 10
ያለፈውን ጥያቄ ኣወ ያከብራል ካሉ ምክንያቱ ለምን ይመስልዎታል?
Answer Count Percentage
ፈረንጂ የሰለጠነ ፍጡር ስለሆነ! 5 3.60%
ፈረንጅ በቀጠሮ የዘገየን ስለማይጠብቅ። 49 35.25%
ኢትዮጵያዊ ከሆነ ግን ስለሚጠብቅ። 20 14.39%
ኢትዮጵያዊ የራሱን ዜጋ ስለሚንቅ። 27 19.42%
ኢትዮጵያዊ ጋር ከሆነ መዘግየት ስለተለመደ። 44 31.65%
Other 8 5.76%

ፈረንጂ የሰለጠነ ፍጡር ስለሆነ!


ፈረንጅ በቀጠሮ የዘገየን
ስለማይጠብቅ።
ኢትዮጵያዊ ከሆነ ግን
ስለሚጠብቅ።
ኢትዮጵያዊ የራሱን ዜጋ
ስለሚንቅ።
ኢትዮጵያዊ ጋር ከሆነ መዘግየት
ስለተለመደ።
Other

አስተያየት፤ ከላይ እንዲሚያዩት ኢትዮጵያዊ ለመጠበቅ ትእግስት አለው፣ ይዘገያል፣ የራሱን ወገን ይንቃል፣ ፈረንጅ
ከሆነ ግን ቀጠሮ የማክበሩ እድል ከፍተኛ ነው። እዚህ ላይ አሻሚ መልሶች ተሰጥተዋል።

Field summary for 11


ቀጠሮ የሚያከብረውን ኢትዮጵያዊ እንደ ፈረንጅ ሆኗል ብለውት ወይም ኣስበው ያውቃሉ?
Answer Count Percentage
ልክ ነው ቀጠሮ የሚያከብር ኢትዮጵያዊ እንደ ፈረንጅ ሆኗል። 11 7.91%
ልማድ ሆኖብኝ ነው እንጂ ኣባባሉ ልክ እንዳልሆነ ኣውቃለሁ። 40 28.78%
በጭራሽ፤ ቀጠሮን ለማክበር የቀጠሮ ባለቤትነት የወሰደ ዜጋ የለም። 49 35.25%
No answer 39 28.06%

ልክ ነው ቀጠሮ የሚያከብር
ኢትዮጵያዊ እንደ ፈረንጅ
ሆኗል።
ልማድ ሆኖብኝ ነው እንጂ
ኣባባሉ ልክ እንዳልሆነ
ኣውቃለሁ።
በጭራሽ፤ ቀጠሮን ለማክበር
የቀጠሮ ባለቤትነት የወሰደ
ዜጋ የለም።
No answer

አስተያየት፤ ስህተት መሆኑንም ቢያውቁት ቀጠሮ የሚያከብርን ኢትዮጵያዊ እንደ ፈረንጅ ሆኗል ብለው የሚያስቡ
ጥቂት አይደሉም። ይህ ማለት አመኑም አላመኑ እንደዛ ማሰባቸው ስለ ቀጠሮ ያላቸውን አስተሳሰብ ከሰው አይነት
እንጂ ከመርሆ ጋር አለመሆኑ ቅር ያሰኛል።
Field summary for 12
ቀጠሮ ከቀጠሩ በኋላ ምን የሚያስቡ ይመስልዎታል?
Answer Count Percentage
ምንም! ብዘገይም ባልዘገይም ቀኑ ሲደርስ እንደፈለኩ መሄድ ብቻ ነው። 9 6.47%
ምንም ችግር የለም! በሰዓቱ እንደምደርስ ኣውቀዋለሁ። 91 65.47%
No answer 39 28.06%

100
80 ምንም! ብዘገይም No answer
ባልዘገይም ቀኑ ሲደርስ
60 እንደፈለኩ መሄድ ብቻ
40 ነው።
ምንም ችግር የለም!
20 በሰዓቱ እንደምደርስ
0 ኣውቀዋለሁ።
1 2

አስተያየት፤ ከላይ እንደሚታየው ከመለሱት ውስጥ ብዙዎቹ በቀጠሮው ለመድረስ በቅድሚያ እንደሚያውቁት
መልሰዋል። አሁንም በብዛት እዚህ መጠይቅ ላይ የተካፈሉት ኢትዮጵያውያን የቀጠሮ ጉዳይ የሚያሳስባቸው
መሆናቸውን ያመለክታል።

Field summary for 13


በቀጠሮ በተደጋጋሚ መዘግየት ኣጠፋው ምንድን ነው ብለው ያስባሉ?
Answer Count Percentage
ምንም የለውም። 4 2.88%
ያሳፍራል። 41 29.50%
ወደጅነትን ሊያሻክር ይችለል። 64 46.04%
መዋሸትም ስለሆነ በእግዜር ወይም በኣላህ ሊያስጠይቅ ይችላል። 20 14.39%
ጥሩ ነገር በወቅቱ ሊታጣ ይችላል። 49 35.25%
Other 5 3.60%

70
60
50 ምንም የለውም። መዋሸትም ስለሆነ በእግዜር
40 ወይም በኣላህ ሊያስጠይቅ
ይችላል።
30 ያሳፍራል። ጥሩ ነገር በወቅቱ ሊታጣ
20 ይችላል።
10 ወደጅነትን ሊያሻክር ይችለል። Other

0
1 2

አስተያየት፤ በቀጠሮ በተደጋጋሚ መዘግየት ወዳጅነትን ሊያሻክር እንደሚችል፣ ጥሩ ነገር በጊዜው ሊያመልጥ
እንደሚችልና እንደሚያሳፍር ብዙዎቹ መልሰዋል።
Field summary for 14
በቀጠሮ መዘግየት ለምን ኢትዮጵያዊ ላይ የባሰ ይመስልዎታል?
Answer Count Percentage
ኢትዮጵያዊ ብዙ ትርፍ ጊዜ ስላለው። 12 8.63%
ኢትዮጵያዊ ጊዜን እንዴት መጠቀም እንደሚችል ገና ስላልነቃ። 60 43.17%
ምናልባት ኣይባስ እንጂ ሌሎችም ዜጎች ይዘገያሉ። 36 25.90%
Other 12 8.63%

70

60
ኢትዮጵያዊ ብዙ ትርፍ
50 ጊዜ ስላለው።
ኢትዮጵያዊ ጊዜን እንዴት
40 መጠቀም እንደሚችል ገና
30 ስላልነቃ።
ምናልባት ኣይባስ እንጂ
20 ሌሎችም ዜጎች
ይዘገያሉ።
10
Other
0
1 2

አስተያየት፤ እዚህ ላይ በርካታ ሰወች ቀጠሮን ብዙ ኢትዮጵያውያን አለማክበራቸው የሚያመለክተው ጊዜን


በትክክል ለመጠቀም አለመንቃት መሆኑን ነው። ይህ ማለት ደግሞ ጊዜን በትክክል ለመጠቀም አለመንቃት
ማለት የስልጣኔ ማነስም ሊሆን ይችላል።

Field summary for 15


በቀጠሮ ከዘገዩና ለምን እንደዘገዩ ሲጠየቁ ምን ይሰማዎታል?
Answer Count Percentage
ይቅርታ እጠይቃለሁ። 76 54.68%
ምክንያቶች እደረድራለሁ። 19 13.67%
ቆጣ ቆጣ ማለት እጀምራለሁ። 0 0.00%
ለቀጠሮ ተብሎ ለምን ሰው እንደሚጨነቅ ኣይገባኝም። 2 1.44%
No answer 42 30.22%

ይቅርታ እጠይቃለሁ። ለቀጠሮ ተብሎ ለምን ሰው


እንደሚጨነቅ ኣይገባኝም።
ምክንያቶች እደረድራለሁ። No answer
ቆጣ ቆጣ ማለት
እጀምራለሁ።

አስተያየት፤ መጠይቁን የመለሱት ሰዎች ቀጠሮ ላይ ለምን እንደዘገዩ ሲጠየቁ ይቅርታ እንደሚጠይቁ
መልሰዋል። ይህ በራሱ ጥሩ ነው። ምክንያትም የሚደረድሩ በርካታ ናቸው። ግን ምክንያት መደርደር
አያስፈልግም።
Field summary for 16
በትንሿ ነገር ካልተለማመድን፣ ነጻነትስ ቢሆን መቼ እናገኛለን! በሚለው ኣባባል ይስማማሉ?
Answer Count Percentage
ኣዎ እስማማለሁ። 51 36.69%
ኣይ ኣልስማማም። 12 8.63%
ሰዎች ከተረዱት ኣባባሉ ጥሩ ነው። 33 23.74%
No answer 43 30.94%

ኣዎ እስማማለሁ።
ኣይ ኣልስማማም።
ሰዎች ከተረዱት ኣባባሉ ጥሩ
ነው።
No answer

አስተያየት፤እዚህ ላይ አዘጋጁ ያሰበው ወይም ማለት የፈለገው ከትንሽ እራስ ቁጥጥር ጋር ሰወች ጥቃቅን
ነገሮችንም እያደረጉ ልምድ ከወሰዱ፣ ከተለማመዱ፣ ትልቅ ነገር ለማድረግም ሊከብዳቸው አይችልም ነው።
ትልቁም ነግር ለምሳሌ እድገት፣ ነጻነትን ማስከበር ወዘተ ሊሆን ይችላል። ለዚህም አንዷ መለማመጃ አጋጣሚ
ቀጠሮ ነች። ታዲያ ተጠያቂዎቹም ይህንን የተረዱት ይመስላል። ብዙዎቹ ልምምድ እንደሚያስፈልግ መልሰዋል።
በርካታዎችም "ሰወች በትክክል ከተረዱት" የሚለውን ስለመለሱ በከፊል በአባባሉ እንደተስማሙ ያሳያል።

Field summary for 17


ኢትዮጵያውያን ቀጠሮ እንዲያከብሩ ምን መደረግ ያለበት ይመስልዎታል?
Answer Count Percentage
ምንም ማድረግ ኣያስፈልግም፣ በዚሁ መቀጠል። 2 1.44%
የሚዘገዩትን መጠበቁን መተው። 66 47.48%
ከተቻለ የሚዘገዩ ሰዎች በሆነ ነገር እንዲቀጡና እንዲማሩ እፈልግ ነበር። 28 20.14%
No answer 43 30.94%
70
60 ምንም ማድረግ
50 ኣያስፈልግም፣ በዚሁ
መቀጠል።
40 የሚዘገዩትን መጠበቁን
30 መተው።
ከተቻለ የሚዘገዩ ሰዎች
20
በሆነ ነገር እንዲቀጡና
10 እንዲማሩ እፈልግ ነበር።
No answer
0
1 2

አስተያየት፤ ለዚህ መልስ ከላይ እንደሚያዩት ቀጠሮ እንዲከበር "የሚዘገዩትን መጠበቁን መተው" ያሉት ብዙ
ናቸው። መቅጫ ቢኖርም ኖሮ የሚዘገዩት እንዲቀጡ የሚፈልጉም ጥቂት አይደሉም። ይህ የሚያመለክተው ቀጠሮ
አክባሪ ኢትዮጵያውያን በማያከብሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ይናደዱባቸዋል ማለት ሊሆን ይችላል።
ማሳሰቢያ፤ ይህንን በተመለከተ አዘጋጁ መጨረሻ ማጠቃለያ ላይ አስቸጋሪነቱን፣ ጥቅምና ጉዳቱንም
ይተነትናል።
Field summary for 18
ፆታዎ ምንድነው?
Answer Count Percentage
ወንድ። 79 56.83%
ሴት። 17 12.23%
No answer 43 30.94%

ወንድ።
ሴት።
No answer

አስተያየት፤ ከሚታየው ቁጥር በላይ ሴቶችም ቢመልሱ ጥሩ ነበር። ሆኖም ግን ጥረት ተደርጓል።

Field summary for 19


እድሜዎ የትኛው ክፍል ውስጥ ነው?
Answer Count Percentage
ከ25 በታች። 7 5.04%
ከ25 በላይ። 89 64.03%
No answer 43 30.94%

100

80

60 ከ25 በታች።
40 ከ25 በላይ።
No answer
20

0
1 2

አስተያየት፤ ቁጥሩ እንደሚያሳየው መጠይቁን የመለሱት 89 ኙ ከ 25 በላይ እድሜ ያለቸ ናቸው። ከ 25 በታች
ግን 7 ብቻ ናቸው። እድሜቸው ከ 25 በታች የሆኑ እኩል የመመለስ እድል እንዳላቸው መልዕክት ተላልፏል።
ምናልባት ኖርዌይ ውስጥ ከ 25 እድሜ በታች የሆኑ ጥቂቶች ናቸው፤ ወይም ኮምፕዩተር ብዙ አይጠቀሙም፤
ስለመጠይቁ በብዛት አልሰሙም፣ መጠይቁ አልሳባቸውም፣ ለመመለስ ጊዜ የላቸውም፣ ወዘተ ሊሆን ይችላል።
Field summary for 20
የሚኖሩበት ሃገር የት ነው?
Answer 96 69.06%
No answer 43 30.94%

መጠይቁ ላይ የተሳተፉት ከዚህ ኣገር ነኝ ባሉት መሰረት በእጅ ተለቅሞ የገባ፤ ብዛት
Norway 74
Sweden 9
Ethiopia 1
America/USA 5
Japan 1
Germany 1
Afganistan 1
Isreal 1
የማይነበብ ኣገር 3
80

70
Norway
60
Sweden
50 Ethiopia
America/USA
40 Japan
Germany
30 Afganistan
Isreal
20
የማይነበብ ኣገር
10

አስተያየት፡ ይህ መጠይቅ እንዲሳካ ኖርዌይ ውስጥ የሚትኖሩ ኢትዮጵያውያን በጣም ትልቅ አስተዋጽኦ
አድርጋችኋል። ያለናንተ ትብብርና ድጋፍ ይህ ውጤት ላይ መድረስ አይቻልም ነበር።
ከልብ አመሰግናለሁ!!!
በመጠይቁ መጨረሻ ላይ ከተሳታፊዎች የቀረቡ አስተያየቶች፤
I have done mine. good luck!
its good collection os question to make Ethiopians aware of time
Thank you Fantish...TATARIW, as usual. you are doing a great Job. This is one of the best ways to
make an attitude change in our society and make our people aware of. Snakkes. Have a great day. S.
Good job
ትልቁ ችግር በቀጠሮ ያረፈዱ ሰዎች እንደሚጠበቁ ስለሚያውቁና ቢያረፍዱ ምንም ዋጋ ካላስከፈላቸው ይዘገያሉ
። ስራ ቦታ ወይም ሃኪም ጋር ግን ሊቀጡ ወይም ገንዘባቸውን ሊከስሩ ስለሚችሉ አይዘገዩም።ስብሰባ ዘገዩም
አልዘገዩም የሚያስከፍላቸው ዋጋ እንደሌለ ስለሚያስቡ ቅር ላይላቸው ይችል ይመስለኛል።
Good questionares
It seems interesting but im little doubtful in that some of the options doesnt reflect the target
questions/too many choices/ and offensiv language use in the options. goood luck!!!!
Question no.15 asks about what I feel if someone asks me about my delay and I think the alternatives
doesnot match the question and becase of the obligation just I answered to go further
ብዙ ጠቃሚ መጠይቆች ቀርበውልናል፡፡ከሁሉም በላይ ደግሞ ያገርዎትን ታሪክ በትክክል ያውቁታል ወይ የሚለውን
መጠይቅ ለወደፊት ብንጠየቅ ደስ ይለናል፡፡

Fak you

it is a meaningful survey
you can call me and ask more about appointment my name is sister tizita million working in the
hospital as a clinical nurse
I think we should lern to respect each other and each othters time. We should be also intoleranet of
those that do not keep there app.time.
Fantaw, please go ahead with your interesting research on other necessary topics as well.
ቀጠሮ እንዳከብር ያስተማረኝ ኢሕአፓ ነው።
መጠይቁ በጣም ጥሩ ጅምር ነው በአግባቡ ከገባንና ከተገበርነው፡፡ግና መጠይቁ ከሌሎች ሀገሮችም ሆነ ሰዎች ጋር
የተዘጋጁት መልሶች ትንሽ ጥናታዊ ዘገባዎችን መፈተሽ ስለሚፈልግ በኢትዮጵያውያን መልሶች ላይ ቢያተኩር
ጥሩ ነበር ፡፡
VERY GOOD IDEA.FIND OUT THE REASON PLEASE.
Please, add for me this....“Unfaithfulness in the keeping of an appointment is an act of clear
dishonesty. You may as well borrow a person's money as his time.” (Horace Mann)
Tatarew: Thank you!
አብዛኛውን አጋጣሚ ባገኘሁ ቁጥር ለመጠቆም ሞክርያለሁ። ባጠቃላይ ይህንና ይህን የመሳስሉት ችግሮችን
ለምን ተፈጠረ? ችግሩ ከታወቀ ደግሞ የችግሩን መፍትሄ መፈለግና ማስተማር ውይም በተገኘው ጊዜና አጋጣሚ
ስበሰባ እየጠሩ መጠቆም ነው። የኢትዮጵያውያኖችን አይኪው ዝቅ የሚያደርገው ይህንና የሄን የመሳስሉ
elementr og livsviktig የሆኑ ነገሮችን ባለመማራችን ነው። ምነአልባት ይህን ጥያቄ ያዘጋጀው ስው ጥሩ
ትምህርት ቤት በመግባት በትምህርት ያገኘው ውይም በተስቦቹ አስተምረውት ይሆናል። ስለዚህ ሌሎች
ኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለው እድል ያለው 1:100000 ስለሆነ ለመርዳትና ለማስተማር ከመሞክር ይልቅ እኔ
ከናንት እሻላለሁ እናንት የማትረቡ ናችሁ ወደሚለው ውይም ኖርዌጅያኖች ajectiv "belære oss"
ወደሚለው ድምዳሜ ስለሚወስድ ለወደፊት ጥያቄዎችህን ፔዳጎጅካል ማድረጉ ውጤታማ ሊሆን ይችላል በዬ
አምናለሁ። ለማንኛውም አንድ ቦታ መጀመር ስላለበት አንተ በዚህ ሁኔታ በመጀመርህ አመስግናለሁ።
i think this very nice specialy we ethiopians must learn about time , i apricisse all you guys what you
preper this god bless you , happy easter
Let us teach our people that time is a precious gift from Jesus in order to use it appropriately and
effectively.
እኔ በጣም የሚያሳዝነኝ ቀጠሮ አለማክበርን እንደጥሩ ባሕል ይዘን መጉአዛችን ነው.ያቃጥለኛል IT IS NOT
BECAUSE I AM LIVING IN WESTERN COUNTRIES BUT THIS IS MY PERSONALITY
STARTING FROM CHILDHOOD WHILE I WAS IN ETHIOPIA
Formulation of some questions might not reflect opinion of the people questioned correctly.Think of
it.
Egziabher yisteh, yh chiger ketekerefelen yeteshekemnew tilku dingay indeweredelen yikoteral. Keza
wedefit lemehed yikelenal. Berta! Amargna fidel selelelegn new yikirta eteyikalhu.
Dear Fantaw, well done and i hope you will get something that will help all of us to respect time.
Thank you for doing this for us.
ketero yemaninet meglecha new.mekeberiya or maferia enigi ethio.or ferenij mehonu lay aydelem.
I belive you need to extend the questionarie, especially the choice - some are really short and limited.
I suggest you review the questions again. otherwise, I admire your initiative and KEEP IT UP!!!
WISH U GOOD LUCK WITH YOUR SURVEY
It is a good start berta
This is a serious and chronic problem of Ethiopians and to address this issue is really excellent. Thank
you and good luck
I don't think Ethiopians will be late for an appointment if it directly concerns them. They are on time
at work, to a doctor, on a payment etc. It is more of a benefit-cost attitude.
It is a nice survey!
Hope to read the result of the survey
ለተነሳሽነትህ እያበረታታሁ ይህ ጉዳይ ከብዙ ያገራችን ውጥንቅጥ ችግሮች ጋር በዓብዛኛ ስለሚያያዝ ሀይማኖቱ
ትምህርቱ ዐጠቃላይ የህብረተሰቡ ከኑሮው ያገኘው ወይም የተለማመደው ነገር ጋር ቁርኝት ዐለው የሚል
አስተሳሰብ አለኝ! መልካም ጥናት ይሆንልህ ዘንድ እመኛለሁ
Hope it will work..Good luck!!..
ቀጠሮ ስለ ማክበር በማንሳትህ አመሰግንሃለሁ። ጊዜ ገንዘብ ነው፣ ሕይወትም ነው። ቀጠሮ ማክበር ራስን ነጻ
የማውጣትና በጊዜ መጠቀመን የተገነዘበ የዘመናዊ ሰው ምልክት ነው።
netedegagami ketero yemayakebro lebotaw beko slalhono, kebudnu meweged yasfelgachewal.
beterefe yehen yemesaselu negeroch, tero erdata slalachew beziho ketel elalehu.
good resurch...
-keeping appointment time need caltural revolution to our feelo citsenshiip. -give awarness to the
people where ever ethiopian are collectd. -make different type of reseach conserning this subject.
-arrange confrance or meeting
Thanks for the wonderful iniciative.
I truly appreciate the effort and it's totally interesting topic. However, I am not sure it's a well-
designed questionnaire because I was stacked in every question. Thank you again for providing me
the opportunity to fill up this form.
ወገናዊ ስላምታዪን እያቀረብኩ ድንቅ ስራ ነው በርቱ እላልሁ ክስላምታ ጋር ሲራጅ
በመጀመሪያ ሀሳቡን አንስቶ የጥናት ጥንስስ መጀመሩ የሚያስመሰግን ነው፡፡ በመቀጠል የመረጃ ማሰባሰቢያ
መጠይቁ የያዘው አማራጮች በአብዛኛው ውስን ናቸው፡፡ ይህ መጠይቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ስላሉ ግለሰቦች ከሆነ
እኔ እንደሚመስለኝ የቀጠሮ ሁኔታ በጣምም ባይሆን በተወሰነ ደረጃ ከብዙ ነገሮች ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምሳሌ-
አጠቃላይ የሀገሪቱ አኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ ሲስተም አዘረጋግ፤ የትምህርት አሰጣጥ፤
የቤተሰብ ሁኔታ፤ የልጅ አስተዳደግ ዘዴ፤ የግለሰቡ የኑሮ ሁኔታ-ስራ፣የትምህርት ደረጃ፣ባህሪ ወዘተ ወዘተ፡፡
በአጠቃላይ ቀጠሮ አያከብሩም በሚባሉ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከዚህ በፊትና አሁን ያለው የቀጠሮ አመለካከት
ከጉዳዩ ክብደትና ጠቃሚነት ጋር በጣም የተገናኘ ይመስለኛል፡፡ ጉዳዩ በተለይ ለራሳቸው ጠቃሚ ከሆነ ከቀጠሮው
ሰዐት ቀድመው የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያ አጋጥመውኛል፡፡ መልካም ጥናት፡፡
የሀበስሻ ቀጠሮ ስለሆነ ምንም አይደል የሚለውን አባባል መዘግየት የሚያዘወትሩ ሰዎች ቢተውትና የጊዜን
አጠቃቀም የበለጠ ቢረዱት ቢተገብሩትም መልካም ነው እላለሁ።
habesha ketro yemyakebrew genzeb yalew sihone new.
arif teyake new
respect time u will be successful in life
NO more
I appriciate your intiative & your hard work.My appology for responding in English.My laptop hasn`t
Amharic soft ware & unable to download which works window 7. Can you help me in this regard.
With profound respect
I do not understand why ?????? Pls. I am eager to know specialy those how lives out Ethiopia thank
you

ውጤቱ ኦስሎ ውስጥ ለኢትዮጵያውያን በአካል በቀረበ ጊዜ የቀረቡ አስተያየቶች፤


የመጠይቁ ውጤት በአውሮፓውያን ሰኔ 19 2010 ላይ በስብሰባ ለኢትዮጵያውያን ቀርቧል። ስብሰባውንም የጠራው
የኢትዮጵያውያን ማህበር በኖርዌይ ነበር። የመጠይቁ ውጤት ከላይ የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ ቀርቧል። ትንሽ
ውይይት ከተደረገ በኋላም አዘጋጁ መጠይቁን በተመለከተ ሁለት ጥያቄዎች ጠይቆ ነበር። እንዚህም "ቀጠሮ
አለመከበሩ የማን ጥፋት ነው? መፍትሄውስ ምንድነው? የሚሉት ናቸው። እያንዳንዱ መላሽ ለሁለቱም ጥያቄዎች
ባንድ ጊዜ እንዲመልስ ወይም ሃሳቡን እንዲሰጥ ተደርጓል። የተሰጡት ሃሳብና መልሶችም ተጨምቀው
እንደሚከተለው ናቸው።

1) የማንም ጥፋት አይመስለኝም፤ ግን በቃ ተፈጥሮአዊ ነው። ሌሎችም ዜጎች ይዘገያሉ።


መፍትሄው የተሳታፊዎች ዝርዝር መላክ ነው። ሰው የሚፈልገውን ነገር መርጦ ስብሰባ መጥራትና የሚዘገዩትን
መጠበቁን መተው።

2) ጊዜን በትክክል መጠቀም ከእድገት ጋር አብሮ የሚሄድ ነው። አፍሪቃ ውስጥ ሰዎች ብዙ የሚያደርጉት ከሌለ
ጊዜንም አያከብሩም። መፍትሄው አገርን ለማሳደግ መጣር ነው።

3) ይሉኝታ ስለሚይዘን ነው እንጂ አድገናል። ጊዜ ባይኖረንም ቀጠሮ እናደርጋለን፤ ግን አናከብረውም። መፍትሄው


ቀጠሮ ወይም ስብሰባ ሲኖረን የሚዘገዩትን መጠበቁን መተው ነው።

4) የሁለቱም ማለት የቀጠሮ ሰጭና ተቀባይ ጥፋት ነው። መፍትሄው በጊዜው ያልመጡትን መጠበቁን መተው።

5) እውነቱን ከመናገር ይልቅ ሁልጊዜ ጥቅም እንፈልጋለን። መፍትሄው ረጅም ስብሰባዎች አለማድረግና የሌሎችን
ፍላጎትና ዝንባሌ ማግኘት።
6) የሁላችንም ሃላፊነት ነው። ባህላችንና ይሉኝታ ነው። መፍትሄው ጊዜን ማክበር፣ እውነቱን መናገርና እርስ በርስ
መከባበር ነው።
7) ጥፋተኛው ስብሰባውን የሚያዘጋጀው ክፍል ነው። መፍትሄውም አዘጋጆች መጀመሪያ እስኪ ጊዜ ያክብሩ!
8) ጥፋተኛው ድህነት ነው። መፍትሄውም ድህነትን መጋፈጥ ነው።

9) ጥፋተኛው አዘጋጁም፣ ተካፋዩም ነው። መፍትሄው ጊዜን ማክበር። መዘግየትን ማሳወቅ። ማስታዎሻ መያዝና
ቀን መቁጠሪያ መጠቀም። የሚዘገዩትን መጠበቁን ማቆም ወይም መቀጣጫ ማድረግ።

10) የምንኖርበት ባህላችን ነው። የኔ እናት አንድ ሰው አርብ እመጣለሁ ካለና ከዘገየ አርብ ሙሉ ስትጠብቀው
ትውላለች። ይህ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በብዙወች ላይ ትልቅ ችግር ነው። መፍትሄው ስብሰባ ሲጠሩ የሰዎችን
ፍላጎት ማወቅና ማረጋገጥ።

11) የማንም ጥፋት አይደለም። መፍትሄው እራስን ለጊዜ እንዲገዛ ማድረግና ምሳሌ መሆን ነው።

አስተያየቶቹንና መጠይቁን መሰረት በማድረግ የታታሪው አስተያየትና ምስጋና፤


የያንዳንዱ የቀጠሮ ጥያቄ ውጤትና አጭር አስተያየት እዛው ከግራፉ ስራ ሰጥቻለሁ። አሁን ደግሞ ማጠቃለያውን
አቀርባለሁ። ትንሽ ማብራሪያም ቢሆን ከመግቢያው ላይ ስለቀጠሮ ማክበር ጠቃሚነት ተጠቅሷል። ኢትዮጵያ
ውስጥ ጊዜ ወርቅ ነው ሲባል ሰምቻለሁ። ውጭ አገር ደግሞ ፈረንጆች ጊዜ ገንዘብ ነው ሲሉ እሰማለሁ። የጊዜ
ውድነት ኢትዮጵያ ውስጥ የበለጠ እየተነገረለት የሚበዙ ኢትዮጵያውያን የቀጠሮ ጊዜን በትክክል አለመጠቀማቸው
አሳሳቢ ነው።

ባጠቃላይ አንድ ሰው ከቀጠሮ በኋላም ሆነ በፊት ብዙ የሚያደርገው ነገር ከሌለ ዘግይቶ ቢደርስም ሆነ ዘግይቶ
ቢጨርስ ለሱ ብዙ ለውጥ የለውም። ይህ ሰው በቋሚነት የሚሰራው ስራ ቢኖርም በትርፍ ጊዜውም ሆነ ቅዳሜና
እሁድ የሚያደርጋቸው የትርፍ ጊዜ ዝንባሌዎች ከሌሉት ብዙ ትርፍ ጊዜ አለው። ይህ ሰው ብዙ ትርፍ ጊዜ ስላለው
የሚያስቸኩል ነገር ወይም በጊዜው የሚደረግና የሚፈጸም ነገር ወይም ጉዳይ ሳይኖረው ይቀራል። እነዚህ
ሁኔታዎች ሰውየውን ጊዜ ላይ እቅድ እንዳያደርግ ያደርጉታል። ስለዚህ ለስብሰባም ሆነ ለሌላ አይነት ቀጠሮ
አሁንም ሆነ በኋላ ቢመጣና ቢሄድ ጊዜው ላይ ችግር አይፈጥርበትም። ይህ ሰው በትርፍ ጊዜው የሚያደርገው ሌላ
ተጨማሪ ዝንባሌ ከሌለው የግለሰቡንም እድገትና የጊዜን ጠቀሜታ ጋር ሲታይ ውስን ያደርገዋል። የግለሰቡንም
የፈጠራ ችሎታውን ሊያሳንሰው ይችላል። በተጨማሪም ይህ ሰው ሌሎችንም ሆነ የሌሎችን ጊዜ አያከብርም።

በትርፍ ጊዜ የሚደረጉ ነገሮች ለምሳሌ አዲስ ነገር ለማወቅና ስለ አለም የበለጠ ለመረዳት መጽሃፍ ማንበብ ሊሆን
ይችላል። የተሰማውንና የሚያውቀውን ነገር መጻፍ ሊሆን ይችላል። የአካልና የመንፈስ እርካታ እንዲሰማው
ስፖርት መስራትና መጸለይ ሊሆን ይችላል። እጅ ለማፍታታትና እራስን ለመፈታተን ምናምን ነገር መቆራቆርና
መጠጋገን ወይም ለመጠገን መሞከርና ማሻሻል ሊሆን ይችላል። በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉ የኮምፕዩተር
ፕሮግራሞችን መለማመድና መስራት ወዘተ ሊሆን ይችላል። በተለያዩ ነገሮች ላይ በሚቻለው መንገድ ሰዎችን
መርዳት ሊሆን ይችላል። እነዚህ እንቅስቃሴዎች ጊዜን በመጠቀምና በማቀድ የሚደረጉ ናቸው። እነዚህ
እንቅስቃሴዎች የዕውቀት መጠንንና ሰብአዊነትንም ይጨምራሉ። አንድ ሰው በተቻለው ሁሉ ጊዜን በመጠቀም
ሰፋ ያለ እንቅስቃሴና ተሳትፎ ከሌለው ለራሱም ሆነ ላካባቢው ያለው ጠቀሜታ አነስተኛ ነው። ስለዚህ የነዚህ
እንቅስቃሴዎች ውስን መሆን አንድ አገር ውስጥ በብዙሃኑ ላይ ከታዩ ያገሪቷንም እድገት ሊገቱት ይችላሉ። አንዲት
አገር ደግሞ ማደግ የምትችለው በዜጋዋ ጥረት ስለሆነ፤ ዜጋዋ ጊዜውን ቁምነገር ላይ ካላዋለው ከጊዜ በኋላ ዜጋው
የሚበላው ምግብ እንኳን ሊያንሰው ይችላል። ነጻም ላይሆን ይችላል። ስለዚህ አንድ ሰው በቀጠሮ የሚዘገየው
የጊዜን ጠቀሜታ ባለመረዳት፣ የሚያደርጋቸውን ነገሮች ከጊዜ ጋር ስለማያመቻች ሊሆን ይችላል።
ለምሳሌ የመጠይቁ ጥያቄ 9፣ 14 ና 1 ላይ እንዳነበቡት ኢትዮጵያዊ ፈረንጅ ጋር ከተቃጠረ በጊዜው ይመጣል
የሚሉት ያደላሉ። ይህ የሚያሳየው ኢትዮጵያዊ ቀጠሮን በተመለከተ የራሱን ወገን አያከብርም ሊሆን ይችላል።
ቀጠሮ አለማክበር ባህሉ ስለተስፋፋም ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳቸው ስለሚተዋወቁ ለጊዜ ግድ የላቸውም ሊሆን
ይችላል። ጥያቄ 14 ላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ቀጠሮ የማያከብረው ጊዜን እንዴት መጠቀም እንደሚችል ገና ስላልነቃ
ነው የሚሉት ያደላሉ። ይህ ደግሞ የሚያሳየው ከላይ በሰፊው እንደተጠቀሰው ኢትዮጵያውያን ጊዜን በእቅድ
በመጠቀም ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ማድረግ እንደሚቻል ገና አልተረዱትም ማለት ሊሆን ይችላል። የጊዜን ጠቀሜታ
መረዳት ቢቻልማ ኖሮ ቀጠሮ በኢትዮጵያውያን መካከል ይከበር ነበር። ጥያቄ ቁጥር 1 ላይም ከበርካታ ምርጫዎች
ውስጥ "ግደለሽነትና ባጋጣሚ መኖር" ብለው የመለሱት ያደላሉ። ይህም የሚያሳየው በርካታ ኢትዮጵያውያን
ጊዜያቸውን የሚጠቀሙት ባጋጣሚ እንጂ በእቅድ እንዳልሆነ ያመለክታል።

ሌላው ዋና ምክንያት ደግሞ ስብሰባም ሆነ የሆነ ዝግጅት ሲኖር ለስብሰባውም ሆነ ለዝግጅቱ ሃላፊነት ያለቸው
ግለሰቦች ወይም መሪዎች ይዘገያሉ። ይህ በሰፊውና በተደጋጋሚ የሚታይ ነው። ለምሳሌ ብዙውን ጊዜ
የሚሰናዳውንም ሆነ የሚቀርበውን ነገር ቦታውና ሰዓቱ ላይ አያቀርቡም። ለራሳቸውም ተዘጋጅተው የማይመጡ
በርካታ ናቸው። በቂ ተካፋዮች ግን በጊዜውና በቦታው መጥተው ይጠብቃሉ። ምናልባት ሰዎች ዘግይተው
የሚመጡት መሪዎቹ አሁን አይጀምሩም (አሁን አይጀመርም) ብለው አስበው ሊሆን ይችላል። ስለዚህ አብዛኛውን
ጊዜ ጥፋቱ ካዘጋጆች/መሪዎች እንጂ የብዙሃኑ ኢትዮጵያውያን አይመስለኝም። መሪዎች ወይም ጉዳዩ
የሚመለከታቸው ግለሰቦች ጊዜን ካላከበሩ ምሳሌ ሊሆኖ አይችሉም። ትንሽም ይሁን ትልቅ ሁኔታ ላይ መሪዎች
ሃላፊነታቸውን ካልተወጡ ብዙሃኑ እምነት ስለማይጥል በጊዜው ላይመጣ ይችላል። ጉዳዩ የሚመለከታቸው ግን
ሲጀመር፣ ሲካሄድና ሲጨረስ ቁጥጥር ኖሯቸው በጊዜውና በእቅድ ካደረጉ፣ ከፈጸሙና ግልጋሎት ከሰጡ ብዙሃኑ
ይህንን ስለሚረዳ ብዙ የሚዘገይ አይመስለኝም። ጥሩ የጊዜ አጠቃቀም ባህልም ሊለመድ ይችላል። በግላችንም
ቀጠሮ ስናደርግ የበለጠ ቀጠሮ አክባሪዎች እንዲንሆን ይገፋፋናል። በትርፍ ጊዜያችንም የተለያዩ ተሳትፎና
ዝንባሌዎችም ካዳበርን ጊዜያችንን ስለሚሻማብን የበለጠ የጊዜ አጠቃቀም እቅድ እንዲኖረን መንገድ ሊከፍት
ይችላል።

ምስጋና!
ይህ መጠይቅ ለዚህ ውጤት የበቃው በተለይ ኖርዌይ ውስጥ ባሉ ኢትዮጵያውያን ትብብር ነው። በእውነት ከልብ
አመሰግናችኋለሁ!! ወደፊትም አንዳንድ ስራዎችን አብረን እንደምንሰራ ሙሉ ተስፋ አለኝ። የኢትዮጵያውያን
ማህበር በኖርዌይ (ኢማኖ) የመጠይቁን ውጤት እንዳስተዋውቅ ስብሰባና ሆኔታወችን ስላመቻቸም አመሰግናለሁ።
ከስዊድንም ሆነ ከሌላ ሃገርም ይህንን መጠይቅ ሞልታችሁ ለመለሳችሁ ሁሉ አመሰግናለሁ።

ፋንታው ተሰማ
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ነሃሴ 2002።

www.tatariw.org
## ጠቃሚ ለመሆን! ##

You might also like